ቡርኪናፋሶ ከአፍሪካ ኅብረት አባልነት ታገደች

ጥር 23/2014 (ዋልታ) የአፍሪካ ኅብረት በቡርኪናፋሶ የተካሄደውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ ሀገሪቱን ከአባልነት ማገዱ ተገለፀ።

ከሳምንት በፊት በሀገሪቱ የተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የነበሩትን ሮህ ማርክ ካቦሬን ከመንበረ ሥልጣን ማስወገዱን የሲጂቲኤን ዘገባ አስታውሷል።