ሐምሌ 10/2013 (ዋልታ) – ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 356 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።
ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።
ተማሪዎቹ በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት መርኃግብሮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው የስትራቴጂክና ኮሙዩኒኬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዘውዱ እመሩ ተናግረዋል።
ከአጠቃላይ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 726 ሴቶች መሆናቸውንም አስታውቀዋል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ተከተል ዮሐንሰና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።