ባለሥልጣኑ ሥርዓተ ፆታን ያገናዘበ የግጭት አዘጋገብ መመሪያ ላይ ከመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች ጋር እየተወያየ ነው

መሐመድ እድሪስ

መጋቢት 30/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከዩኤን ውሜን ኢትዮጵያ ጋር በመተባባር ሥርዓተ ፆታን ያገናዘበ የመገናኛ ብዙኃን የግጭት አዘጋገብ መመሪያ አዘጋጅቶ ከመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች ጋር እየተወያየ ነው፡፡

ውይይቱም የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ከግጭት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ዘገባዎች በሚዘግቡበት ጊዜ ሥርዓተ ፆታ ላይ የተመረኮዙ ጅምላ ፍረጃዎችን፣ የተዛቡ ሥርዓተ ፆታዊ አስተሳስቦችን እና አድሎዎችን እንዲያስወግዱ እንዲሁም ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ የግጭት ዘገባ አቀራርቦችን እንዲገነዘቡ እና መመሪያውን ተከትለው እንዲሰሩ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እድሪስ የፆታ እኩልነት የወንዶችና ሴቶችን ድምፅ በእኩል መጠን ለማስተናገድ እንዲያመች ሥርዓተ-ፆታን ያገናዘበ የግጭት አዘጋገብ መመሪያ መዘጋጀቱንና ይሄን ለማስፈፀም የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተጨማሪም ለባለሙያዎቹ ተከታታይ የሆነ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት እንደሚያስፈልግ ገልፀው ተሳታፊዎቹ ከስልጠናው ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሚያስችላቸውን ልምድ እንደሚያገኙበት ማናገራቸውን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW