ባለስልጣኑ ሮም የገበታ ጨው ምርቶችን ከገበያ እየሰበሰበ መሆኑን ገለፀ

ግንቦት 12/2014 (ዋልታ) ሮም የገበታ ጨውንና ሴንሆን የማር ምርቶች ከገበያ እየሰበሰበ መሆኑን የአዲስ አበባ ምግብ፣ መድኃኒት፣ ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።
ሮም የገበታ ጨውና ሴንሆን የምርት ውጤቶች ተገቢውን የጤና ብቃት ማረጋገጫ ሳያወጡ ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ በመስራታቸውና የምርቶቹ ናሙና ተወስዶ በላብራቶሪ ሲመረመር መስፈርቱን ያላሟሉ በመሆናቸው ድርጅቶች ታሽገው ምርቶቹን በሁሉም ክፍለ ከተሞች ከገበያ እንዲሰበሰቡ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የተሰበሰቡት ምርቶችም መመሪያውን በተከተለ መልኩ እንደሚወገዱ ተገልጿል፡፡