ባለስልጣኑ በጦርነት ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ800 ሺሕ ብር በላይ የሚገመት የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ

ኅዳር 24/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን “ምሳችንን ለወገናችን” በሚል በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ800 ሺሕ ብር በላይ የሚገመት የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉ የተሰባሰበው ከባለስልጣኑ ዋናው መስሪያ ቤት፣ ከሁሉም ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች፣ ከፕሮጀክት ጽህፈት ቤት እና መሰረታዊ የሰራተኛ ማኅበር አመራሮች እና ሰራተኞች ነው ተብሏል፡፡

የተደረገው ድጋፍም ፍራሽ፣ ብርድ ልብስ፣ ፓስታ፣ ማካሮኒ፣ ሩዝ፣ ዘይት፣ ዱቄት፣ ጨው፣ በርበሬ፣ የሕፃናት አልሚ ምግቦች፣ የሕፃናት እና የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ እና ሳሙና መሆናቸው ተመላክቷል፡፡ በተጨማሪም የወንድ፣ የሴት፣ የህጻናት ልብስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

የባለስልጣኑ አመራሮችና ሰራተኞች ያሰባሰቡትን ድጋፍ ለአዲስ አበባ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ዋና አስተባባሪ ሰለሞን ፍሰሃ አስረክበዋል፡፡

በተስፋዬ አባተ