ባንኩ ለህዳሴ ግድብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ መተግበሪያ ድረ ገጽ ይፋ አደረገ

ሐምሌ 28/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ መተግበሪያ ድረ ገጽ ይፋ አድርጓል፡፡

“itismydam.et” የተሰኘ ድረ ገጽ አዲስ የዲጅታል መተግበሪያ ይፋ የተደረገ ሲሆን  በውጭ ሀገር ለሚኖሩ የግድቡ ተሳታፊዎች ምቹ እና በቅርበት የሚገኝ ይሆናል ተብሏል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና ዳይሬክተር አቤ ሳኖን፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል  ዋና ስራ አስፈጻሚ አሸብር ባልቻ እና የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ተገኝተዋል፡፡

(በአመለወርቅ መኳንንት)