ባንኩ ሴት ሙዚቀኞችና ገጣሚዎችን ሸለመ

ሚያዝያ 12/2014 (ዋልታ) አቢሲኒያ ባንክ “እችላለሁ” በሚል መሪ ሃሳብ በሴቶች የሙዚቃና የግጥም ውድድር ሲያወዳድራቸው የነበሩ አሸናፊዎችን ሸለመ።

በዚህም በሁለቱም ዘርፎች ለአንደኛ አሸናፊ 50 ሺሕ ብር ለ2ኛ አሸናፊ የ30 ሺሕ ብር እንዲሁም ለ3ኛ አሸናፊ የ20 ሺሕ ብር ሽልማት አበርክቷል።

በሌላ በኩል የመርኃ ግብሩ ሌላኛው አካል በነበረው የሥራ ፈጣሪዎችን የብድር ጥያቄ በማወዳደር ለአሸናፊዎች ከገበያው ባነሰ ወለድ ምጣኔና ካለመያዣ እስከ 300 ሺሕ ብር ድረስ ብድር እንደተመቻቸ ተጠቁሟል፡፡

በዚህም ጥያቄ ካቀረቡት 387 አመልካቾች መካከል 27 የሥራ ፈጣሪዎች የተለዩ ሲሆን በየአቅራቢያቸው ባሉ ዲስትሪክቶች አማካኝነት በቅርቡ የብድር አገልግሎት እንደሚያገኙ ባንኩ አስታውቋል፡፡

ባንኩ የተለያዩ የባንክ አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ ሴቶችን እያበረታታ እንደሚገኝም ተገልጿል።

በእመቤት ንጉሴ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW