ባንኩ 41 ቢሊዮን ብር ሀብት እንዳለው ገለጸ

ሰኔ 5/2014 (ዋልታ) ወጋገን ባንክ 41 ቢሊዮን ብር ሀብት እንዳለው ገለጸ።

ባንኩ የተመሠረተበትን 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ሲያከበር ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ለመቄዶኒያ እና ለጌርጌሶን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከላት ለእያንዳንዳቸው የ250 ሺሕ ብር ድጋፍ አድርጓል።

የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ ይናገር ደሴ በፈታኝ ጊዜያት ጤናማ እንቅስቃሴ ካደረጉ ባንኮች አንዱ ወጋገን መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የወጋገን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አብዲሹ ሁሴን ወጋገን ባንክ ከ25 ዓመታት በፊት ሲመሰረት በ60 ሚሊየን ካፒታል እና በ13 ሠራተኞች እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡

ዛሬ ላይ ካፒታሉን 5 ነጥብ 6 ቢሊዮን በማድረስ የሠራተኞቹን ቁጥርም 5 ሺሕ ማድረስ መቻሉን ተናግረዋል።

በሳራ ስዩም