ብልፅግና ፓርቲ ባሳለፋቸው ውሳኔዎች ላይ የሚመክር ጉባዔ በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው

መጋቢት 14/2014 (ዋልታ) በጋምቤላ ክልል በአኙዋክ ብሔረሰብ ዞን በአቦቦ ወረዳ ከተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር የብልጽግና ፓርቲ ድህረ ጉባዔ የህዝብ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የጋምቤላ ክልል ዋና አፈ ጉባኤ ባንቻየሁ ድንገታ፣ ውይይቱ ብልፅግና ፓርቲ በጉባዔው ያሳለፋቸውን ውሳኔዎችና አቋሞች ህዝቡ እንዲገነዘባቸው እና ለተፈፃሚነታቸውም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ አቅም ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል፡፡

ብልፅግና ህብረተሰቡን ከድህነት ለማውጣት እየሰራ እንደሚገኝ የገለፁት አፈ ጉባኤዋ፣ ህብረተሰቡ ተማምኖበት የመረጠው እስከሆነ ድረስ ተያይዞ ለማደግ የሕዝብ ተሳትፎ አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የአኙዋክ ብሔረሰብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኡቦንግ ኡጁሉ በበኩላቸው፤ ፍትሀዊ እና አካታች የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ብልጽግና ትልቅ ዕድል መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል፡፡