ብሔራዊ የመንገድ ደኅነንት የአስር ዓመት ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

ሐምሌ 8/2014 (ዋልታ) የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ያለውን የመንገድ ደኅንነት ያሳልጥልኛል ያለውን በትራፊክ አደጋ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የአስር ዓመት ብሔራዊ የመንገድ ደኅነት ስትራቴጂ ይፋ አድርጓል።

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ዴኤታ በርኦ ሀሰን የዓለም ዐቀፍ ሁኔታዎችና የኢትዮጵያን ተሞክሮ በማቀናጀት የተቀረፀው ስራቴጂ በመንገድ ደኅንነት ላይ ለውጥ እንደሚያመጣ ተናግረዋል።

ስትራቴጂው በ10 ዓመቱ ትግበራው በመንገድ ትራፊክ አደጋ የሚደርሰውን ሞት በ50 በመቶ ለመቀነስ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ባለፉት 3 ዓመታት በትራፊክ አደጋ በ10 ሺሕ ተሽከርካሪዎች የሞት መጠኑ 32 ነጥብ 6 በመቶ እንደነበር ተጠቁሞ በአስር ዓመቱ ስትራቴጂካዊ ትግበራ ወደ 10 በመቶ ለማውረድ መታቀዱ ተገልጿል።

ለትራፊክ አደጋ መንስኤ የሆነው የአሽከርካሪነት መንጃ ፈቃድ አሰጣጥ ወጥ እንዲሆን በሀገር ዐቀፍ ደረጃ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ሥርዓት ከሁለት ዓመታት በኋላ ተግባራዊ እንደሚሆን ተነስቷል፡፡

በዓለም ዐቀፍ ደረጃ በየዓመቱ 1 ነጥብ 35 ሚሊዮን ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ያልፋል፡፡

በምንይሉ ደስይበለው