ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ በተባበሩት አረብ ኢሚሬት ፕሬዘዳንት ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ በተባበሩት አረብ ኢሚሬት ፕሬዘዳንት ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ፡፡

ሼህ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን የተባበሩት አረብ ኢሚሬትን ወደ ስልጣኔ ጎዳና የመሩ፣ አረብ ኢሚሬትን የበረሃ ገነት ያደረጉ እና የአባታቸውን ፈለግ በመከተል እስልምናቸውንም ያጠናከሩ ብልህ ሰው እንደነበሩ ገልጸዋል።

ሟቹ አዲስ አበባ የሚገኙ የቄራ መስጊድና ፒያሳ ያለው በኒን መስጊድን በአባታቸው ስም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሠሩ ደግ ሰው እንደነበሩም በሀዘን መልዕክታቸው አስታውሰዋል።

ሼህ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW