ተባብረን ከሰራን የበለጸገች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን እንደምናስረክብ ምንም ጥርጥር የለውም – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ሰኔ 22/2016 (አዲስ ዋልታ) ተባብረን ከሰራን የበለጸገች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን እንደምናስረክብ ምንም ጥርጥር የለውም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ በደሴ ከተማ እና አካባቢው እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረን ተመልክተናል ብለዋል።

ከደሴ ከተማ ከተውጣጡ ነዋሪዎች ጋር መገናኘታቸውንም የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁሉም ቦታ እጅግ አመርቂ የሆኑ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አረጋግጠናል ነው ያሉት።

ተባብረን ከሰራን የበለጸገች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን እንደምናስረክብ ምንም ጥርጥር የለውም ሲሉም በመልዕክታቸው አስገንዝበዋል።