ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ እውነታዎች
- የግድቡ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የተጣለው፡- መጋቢት 24/2003 ዓ.ም በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አማካኝነት
- የሚገኝበት ስፍራ፡- ግድቡ በአባይ ወንዝ ላይ የተገነባ ሲሆን፣ የሚገኘው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ ነው፡፡
- ፕሮጀክቱ ያካተታቸው ሦስት ሥራዎች፡- የሲቪል ስራዎች ( civil works ) አሌክትሮ መካኒካል እና ሃይድሮሊክ ስቲል ስትራክቸር ሥራዎች (Electromechanical & hydraulic steel structures ) እና ለግድቡ ስራ መኖሪያቸውን የለቀቁትን ሰዎች ማስፈርና ማቋቋም ናቸው፡፡
- እንዲጠናቀቅ የታቀደለት ጊዜ፡- የግድቡ ስራ ሲጀመር በ6 ዓመት ጊዜ ውስጥ በ80 ቢሊዮን ብር ወጪ እንዲጠናቀቅ ታቅዶ ነበር፡፡
- የህዳሴ ግድብ ሦስት አካላት
ዋነኛው ግድብ፡-145 ሜትር ከፍታ እና1780 ሜትር ርዝማኔ አለው፡፡
ግድቡ ግራና ቀኝ የሚገኙት ሁለት የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች፡-13 ተርባይን ጀነሬተሮችን ያካተቱ ሲኖን፣በአጠቃላይ5150 ሜጋዎች እና15760 ጃጋዋት ሰዓት በዓመት የማመንጨት አቅም አለው፡፡
የኮርቻ ግድብ (saddle Dam)፡-50ሜትር ቁመት እና 5200ሜትር ርዝማኔ አለው፡፡
- ግድቡ ሲጠናቀቅ የሚይዘው የውሃ መጠን፡-74 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ
- ውሃው የሚተኛበት ስፍራ ስፋት፡-1874 ካሬ ኪሎ ሜትር ሲሆን ውሃው ከግድቡ ወደ ኋላ 240ኪሎ ሜትር ይረዝማል፡፡
- የግድቡ ስራ በሚጠናቀቅበት ጊዜ ትልቅ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ይፈጠራል፡፡
- የመልሶ ማቋቋም ስራ፡- ከግድቡ ግንባታ ጋርበተያያዘ፣የመኖሪያ ስፍራቸውን የቀየሩ 5390 አባወራዎችና እማወራዎችን መልሶ የማስፈር፣የማቋቋም እና የመሰረተልማት ግንባታ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡
ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር የተያያዙ ያላላቅ ሁነቶች
- ግንቦት 2005 የአባይ ወንዝ አቅጣጫ ለመጀመሪያ ጌዜ ተቀየረ፡፡
- መጋቢት 2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ፣ግብፅ እና ሱዳን መካከል የሶስትዮች የመርሆች ስምምነት ተፈረመ፡፡
- ሃምሌ 2012 እና ነሀሴ 2013 ዓ.ም ኢትዮጵያ የመጀመሪያ እነ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌቶችን አሳክታለች፡፡*
- እስካሁን ለግድቡ ግንባታ ከ163 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ወደ163 ቢሊዮን ብር ከሕዝባዊ መዋጮ የተገኘ ነው፡፡
- የታላቁ ህዳሴ ግድብ ወጪ እስካሁን ሙለ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት እና ሕዝብ የተሸፈነ ሲሆን በቀጣይነትም ኢትዮጵያውያን በተባበረ ክንድ ያጠናቅቁታል፡፡
ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት