ቻይና በሰሜን ኢትዮጵያ ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚሆን ከ2 ሺሕ ቶን በላይ የሰብኣዊ እርዳታ ለገሰች

የካቲት 02/2014 (ዋልታ) ቻይና በሰሜን ኢትዮጵያ ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚሆን ከ2 ሺሕ ቶን በላይ የሰብዓኣዊ እርዳታ ድጋፍ ማድረጓን የቻይና ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

የቻይና መንግሥት ለኢትዮጵያ ያደረገው አስቸኳይ የሰብኣዊ እርዳታ በሰሜን ኢትዮጵያ ለተፈናቀሉ ወገኖች እየተከፋፈለ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የተደረገው ድጋፍ ሁለቱ አገራት ያላቸውን ጥልቅ ወዳጅነት የሚያመለክት መሆኑን ስለመግለፁም ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡