ነገ በሁሉም የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የጽዳት ዘመቻ እንደሚካሄድ ተገለፀ

ጥር 21/2014 (ዋልታ) ነገ በሁሉም የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የጽዳት ዘመቻ እንደሚካሄድ የክልሉ የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮ ኃላፊ ጉዮ ገልገሎ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ከተሞችን ውብ፣ ጽዱና ለነዋሪዎች ሚቹ ለማድረግ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ነገ ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ አካባቢውን እንዲያጸዳ ጥሪ አቅርበዋል።
ይህ የጽዳት መርኃግብር ተጠናክሮ የሚቀጥል እና ወር በገባ በሶስተኛው ሳምንት ቋሚ የጽዳት ዘመቻ እንደሚካሄድ ገልፀዋል።
ኅብረተሰቡ አካባቢውን የማጽዳት ባህሉን በማሳደግ ከተሞችን ማስዋብ እንደሚገባም ኃላፊው አሳስበዋል።
በአሳንቲ ሀሰን