ነገ 21 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል

የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በዓል

ሚያዝያ 26/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ በነገው ዕለት 21 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ነገ የሚከበረውን የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በዓልን በማስመልከት ነገ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መድፍ የሚተኮስ መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

የመከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ ፖሊስ ዳይሬክቶሬት ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ መድፉ ለበዓሉ ክብር የሚተኮስ መሆኑን ገልጿል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW