አሜሪካ ጦሯን ከአፍጋኒስታን ለማስውጣት ወታደራዊ ኃይል አሰማራች

ሚያዝያ 29/2013 (ዋልታ) – አሜሪካ ከአፍጋኒስታን ለሚወጡት የአሜሪካ እና ለጥምር ጦሩ ሽፋን የሚሰጥ ወታደራዊ ኃይል አሰማራች።
አገሪቷ ወታደሮችን እና ሲቪል ሠራተኞችን ለመጠበቅ ቦምብ ጣይ እና ተዋጊ አውሮፕላኖች መመደቦ ተነግሯል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የመስከረም 11 ጥቃት 20ኛ ዓመት መታሰቢያ ዕለት የአሜሪካ ጦር ከአፍጋኒስታን ሙሉ
በሙሉ እንደሚለቅ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።
በዚህም የጦሩ መውጣት ዜና ከተሰማ ጀምሮ ጥቃቶች የበረከቱ ሲሆን የአፍጋኒስታን የጸጥታ ኃይሎች የበቀል እርምጃ ይኖራል በሚል በተጠንቀቅ ቆመዋል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።
ታሊባን ዓለም አቀፍ ወታደሮችን ዒላማ እንዳያደርግ የተደረሰበት ስምምነት እንደማይገዛው አስጠንቅቋል።
ታጣቂዎቹ እና ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ባለፈው ዓመት በተፈራረሙት ስምምነት መሠረት ታሊባን ዓለም አቀፍ ወታደሮችን የማያጠቃ ሲሆን የውጭ ኃይሎች ደግሞ እስከ ግንቦት 1 ቀን መልቀቅ ነበረባቸው ተብሏል።
አሜሪካ እና ኔቶ በአፍጋኒስታን ለ 20 ዓመታት ያህል ቆይተዋል።