አምባሳደር ሀሰን ታጁ ከኩዌት ረዳት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአፍሪካ ጉዳዮች ሀላፊ ጋር ተወያዩ

ሚያዚያ 13/2014 (ዋልታ) በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር አምባሳደር ሀሰን ታጁ ከኩዌት ረዳት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአፍሪካ ጉዳዮች ሀላፊ አምባሳደር ሱለይማን ዐሊ ሰዒድ ጋር ተወያይተዋል።

በዉይይቱ ወቅት አምባሳደር ሀሰን ስለኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ ሁለቱ ሀገራት በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በቱሪዝም፣ በትምህርት፣ በባህልና በሌሎች መስኮች ትብብራቸዉን ይበልጥ በሚያሳድጉበት ዙሪያም ሀሳብ መለዋወጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል።