አምባሳደር ሃደራ አበራ ኢትዮጵያዊያን በአገራቸው ወቅታዊ ጉዳዮች ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቀረቡ

ግንቦት 23/2013 (ዋልታ) – በጋና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሃደራ አበራ በጋና፣ አክራ ከሚኖሩ አምባሳደር ሃደራ አበራ በጋና የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአገራቸው ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በወቅቱም አምባሳደሩ ሀገራችን በአሁኑ ወቅት በሀገር ውስጥና ከውጭ ያጋጠሟትን የተለያዩ ፈተናዎች ለኮሚኒቲው አባላት በዝርዝር አስረድተዋል።
አያይዘውም ሚሲዮኑ ተልዕኮው ለመወጣት የሚያደርገው እንቅስቃሴ ስኬታማ እንዲሆን የኮሚኒቲው አባላት ድጋፍና ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን በመግለጽ፣ ከሁሉም ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር የሀገራችንን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ዙርያ ተባብረው ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
(ምንጭ፡-የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ )