አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ከሳዑዲ ፈንድ ለልማት ዋና ኃላፊ ጋር ተወያዩ

                              አምባሳደር ሌንጮ ባቲ

ሰኔ 24/2013 (ዋልታ) – በሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ከሳዑዲ ፈንድ ለልማት ዋና ኃላፊ ሱልጣን አል ማርሻድና ከሳዑዲ ፈንድ የኦፕሬሽን ዳይሬክተር ጄነራል ኢንጅነር ፈይሰል አል ቀጣን ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይቱ በሁለትዮሽ ግንኙነት፣ የኢትዮጵያ እና የሳዑዲ ፈንድ ድርጅት የጋራ የኢኮኖሚ ልማት ትብብር ዙሪያ መክረዋል፡፡

እንዲሁም በቀጣይ የኢትዮ-ሳዑዲ ሁለትዮሽ ግንኙነቱ እንዲሁም የሳዑዲ ፈንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያለው የልማት ትብብር በሚጠናከርበት ዙሪያ፣ የኢኮኖሚ እድገትን ሊያፋጥኑና ህዝብን ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ አዳዲስ የትብብር መስኮች በመለየት መስራት በሚቻልበት ዙሪያም ውይይት ማድረጋቸውን ከሳዑዲ አረብያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡