አምባሳደር ረታ ዓለሙ ከእስራኤል ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ

አምባሳደር ረታ ዓለሙ

ኅዳር 10/2014 (ዋልታ) በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ረታ ዓለሙ ከእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በወቅቱም በአገራችን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታዎች እና የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚመለከት ምክክር አድርገዋል።

ፕሬዝዳንት ሄርዞግ እስራኤል እንደ ወዳጅ አገር ለኢትዮጵያ ያላትን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል።

በውይይቱ ወቅትም ለኢትዮጵያ የአጋርነት መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።