አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በፀጥታው ምክር ቤት ምን አሉ ?

ነሀሴ 21/2021 (ዋልታ) – በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልእክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የህወሓትን ጸብ አጫሪነት ለምክር ቤቱ አብራሩ ፡፡

የኢትዮጵያ መንግሰት ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ የተናጠል ተኩስ አቁም አውጆ ከትግራይ መውጣቱን የገለጹት መልእክተኛው ተኩስ አቁሙ የተደረገው በአካባቢው የሰብአዊ እርዳታ እንቅቃሴ እንዲሳለጥ ለማድረግና ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት ነበር ብለዋል።

ነገር ግን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተሰየመው ህወሓት ወደ ተኩስ አቁሙን ለመቀበል  ፍላጎት ስለሌለው  ህጻናትን ወደ ውትድርና እያስገቡ ነው፤ ወላጆች ልጆቻውን ለውትድርና እንዲሰጡ እርዳታ እህልን እንደ ማስፈራሪያ እየተጠቀሙ ነው ብለዋል።

ህወሓት በአማራ እና በአፋር ክልሎች ላይ በከፈተው ጥቃት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀለቸውን የገለጹት አምባሳደር ታዬ በህወሓት ተግባር ከትግራይ ክልል በተጨማሪ በአማራና አፋር ክልሎች የሚገኙ አርሶ አደሮች የግብርና ስራ መስራ እንዳልቻሉም አድርጓል ሱሉ አስረድተዋል።

ቡድኑ የእርዳታ እህሎች እንቅስቃሴን እያስተጓጎለ መሆኑን የጠቀሱት አምባሳደር ታዬ  ሀገሪቱ እንዳትረጋጋ ከተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀይሎች ጋር ጥምረት እየፈጠረ መሆኑን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ግብ ሰላም ነው፤ ነገር ግን ህወሓት በኢትዮጵያ ሰላም እንዳይሰፍን እንቅፋት ሆኖ ቆሟል ሲሉም ተናግረዋል።

ሁሉም ሰላም ወዳድ አካል ህወሓትን ከሽብር ተግባሩ እንዲታቀብ ጫና እንዲፈጥር ጥሪ አቀርባለው ብለዋል አማባሳደር ታዬ ፡፡ ሁሉም የም/ቤቱ አባላት እውነታ ላይ የተመሰረተ መረጃ ብቻ እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ በልዩነት ውስጥ አንደነትን መፍጠር የቻለች ሀገር ነች ያሉት አምባሳደር ታዬ አሁን በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለው ለውጥ መድሎን ሳይሆን አንድነትን ማጠናከር ላይ ያተኩራል ብለዋል።