አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው የኢትዮጵያ ቡና በአልጄሪያ ገበያ ስለሚቀርብበት ሁኔታ መከሩ

ግንቦት 15/2014 (ዋልታ) በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው የኢትዮጵያ ቡና በአልጄሪያ ገበያ ስለሚቀርብበት ሁኔታ በሀገሪቱ እውቅ ከሆነው የቡና አቅራቢ ፌኔክ ኮፊ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ።

አምባሳደር ነቢያት በአልጄሪያ የቡና አቅርቦት ዘርፍ ባለ ልዩ ጣዕም ቡና አቅራቢ ከሆነው ፌኔክ ኮፊ ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።

በውይያታቸውም የኢትዮጵያ ባለ ልዩ ጣዕም ቡና ቀጥታ ወደ አልጄሪያ ገበያ ስለሚቀርብበት ሁኔታ መምከራቸውን አምሳደሩ አስታውቀዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

ኢትዮጵያ ባለፉት 10 ወራት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ውጭ ከተላከ ቡና አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንዳገኘች መገለጹ ይታወሳል።