አምባሳደር ካሳ ከበደ አረፉ

ታኅሣሥ 17/2014 (ዋልታ) አምባሳደር ካሳ ከበደ ማረፋቸውን ያሳወቀው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለፀ።
አምባሳደር ካሳ በጄኔቫ የኢትዮጵያ አምባሳደርነትን ጨምሮ በሌሎችም ከፍተኛ ኃላፊነቶች አገራቸውን አገልግለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለቤተሰባቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውና የቀድሞ የሥራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል።