አምባሳደሮች ለኢትዮጵያ ክብር እና ሉኣላዊነት የሚጠበቅባቸውን ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተናገሩ

ኅዳር 17/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት የወከሉ አምባሳደሮች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ለአገራቸው ክብር እና ሉኣላዊነት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተናገሩ።

አምባሳደሮቹ እና የሚኒስቴሩ የሥራ ኃላፊዎች ይህን ያሉት እየተካሄደ ባለው ዓመታዊ ስብሰባቸው ላይ ነው ።

“እኛ ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት የወከልን አምባሳደሮች የአገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ወቅቱ የሚጠብቀውን የዲፕሎማሲ ሥራ እየሠራን ከመሪያችን፣ ለአገራችን ክብር ከሚዋደቀው የአገር መከላከያ ሰራዊት እና ከመላው የፀጥታ ኃይላችን ጎን መቆማችንን ስንገልፅ ታላቅ ኩራት እና ክብር ይሰማናል ” ነው ያሉት።

ዲፕሎማቶቹ በቀጣይም የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸው ገልፀዋል፡፡
ለአገር መከላከያ ሰራዊት የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በነገው ዕለትም ደም እንደሚለግሱ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡