አርቲስት ዘነቡ ገሠሠ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

አርቲስት ዘነቡ ገሠሠ

ሚያዝያ 17/2014 (ዋልታ) አርቲስት ዘነቡ ገሠሠ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡

አርቲስት ዘነቡ ገሠሠ የሁለት ሴቶች እና የሁለት ወንድ ልጆች እናት የነበረች ስትሆን ባደረባት የጡት ካንሰር ህመም በሕክምና ስትረዳ ቆይታ በዛሬው ዕለት ሕይወቷ ማለፉ ነው የተሰማው፡፡

የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ነገ ሚያዝያ 17 ቀን 2014 ዓ.ም.
ከቀኑ 9:00 ሰዓት በቡልቡላ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም ለማወቅ ተችሏል።

አርቲስት ዘነቡ ገሠሠ በርካታ የጥበብ ሥራዎች ላይ በመሳተፍ እና ድንቅ ብቃቷን በማሳየት አድናቆትን አትርፋለች፡፡

ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት በአርቲስቷ ሞት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለወዳጅ ዘመዶቿ እና ለአድናቂዎቿ መፅናናትን ይመኛል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW