አስተዳደሩ ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን የሚቀበልበት የስልክ ቁጥሮችን ይፋ አደረገ

መጋቢት 16/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከኅብረተሰቡ የተለያዩ ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን የሚቀበልበት የስልክ ቁጥሮችን ይፋ አድርጓል፡፡
አስተዳደሩ ከኅብረተሰቡ ጋር ውይይቶችን ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
በዚህም ከኅብረተሰቡ በርካታ ጠቃሚ ሃሳቦችንና ግብዓቶችን ማሰባሰብ ተችሏል፡፡
ሆኖም አሁንም ኅብረተሰቡን ለማዳመጥ ተጨማሪ አማራጮችን መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ ማንኛውም ሰው ካለበት ሆኖ ጥቆማዎችን መስጠት የሚችልበት የስልክ ቁጥሮችን አስተዳደሩ ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
አጭር ቁጥር ፡- 9977
የሞባይል ስልኮች
09-00640830
09-00640789
አስፈላጊ የሰነድ መረጃዎችን በቴሌግራም መተገበሪያ ለማያያዝ እና ለአጭር የፅሑፍ መልእክቶች የሞባይል ቁጥሮችን መጠቀም እንደሚችሉ የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።