አሸባሪው ሕወሓት ዳግም የከፈተውን ጦርነት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ ሊካሄድ ነው

ነሐሴ 26/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ሕወሓት ዳግም የከፈተውን ጦርነት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

ሰልፉ “በአገር ሕልውናና አንድነት አንደራደርም!” በሚል መሪ ሀሳብ ማክሰኞ ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ.ም በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት እንደሚካሄድ ኢዜአ ከሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ግብረ ኃይል ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሰልፉ አሸባሪው ሕወሓት ዳግም የከፈተውን ጦርነት ለማውገዝና የአገርን ሕልውና ለማስጠበቅ እየተሳተፉ ላሉ ለአገር መከላለከያ ሰራዊት፣ ለጸጥታ ኃይሎችና ዜጎች ድጋፍና አጋርነትን የመግለጽ አላማ እንዳለውም ተመልክቷል።

ግብረ ኃይሉ ሰልፉን ከአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጋር በትብብር እንዳዘጋጀውም ተገልጿል።