አሸባሪ ሕወሓትን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ በዋሺንግተን ዲሲ ይካሄዳል

አሸባሪ ሕወሓትን የሚያወግዝ ሰልፍ

ጳጉሜ 1/2014 (ዋልታ) በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ አሸባሪው ሕወሓት ዳግም የከፈተውን ጦርነት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ ይካሄዳል።

ሰልፉ “በአገር ኅልውናና አንድነት አንደራደርም!” በሚል መሪ ሀሳብ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት እንደሚካሄድ ከሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ግብር ኃይል ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።

ሰልፉ አሸባሪው ሕወሓት ዳግም የከፈተውን ጦርነት ለማውገዝና የአገርን ኅልውና ለማስጠበቅ እየተሳተፉ ላሉ ለአገር መከላለከያ ሰራዊት፣ ለጸጥታ ኃይሎችና ዜጎች ድጋፍና አጋርነትን የመግለጽ አላማ እንዳለው ገልጿል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ሌሎች የኢትዮጵያ ወዳጆች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በአሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት በሰልፉ ላይ በመሳተፍ አጋርነታቸውን እንዲያሳዩም ጥሪ ቀርቧል።

የሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ግብር ኃይል ሰልፉን ከአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ጋር በትብብር እንዳዘጋጀውም ተገልጿል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW