አቢሲንያ ባንክ ለዳግማዊ ሚኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል 2 የኩላሊት እጥበት መሳሪያዎችን አስረከበ

የካቲት 5/2014 (ዋልታ) “ማኅበራዊ ኃላፊነትን መወጣት ዕሴታችን ነው” በሚል መርህ አቢሲንያ ባንክ ለዳግማዊ ሚኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል 2 የኩላሊት እጥበት መሳሪያዎችን እና ለኩላሊት ህክምና የሚሆኑ ሌሎች መሳሪያዎችን አስረከበ።

የኩላሊት እጥበት መሳሪያዎቹን የአቢሲንያ ባንክ ፕሬዝዳንት በቃሉ ዘለቀ ለሆስፒታሉ አስረክበዋል።

የዳግማዊ ሚኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ታደሰ ስለተደረገው ድጋፍ አመስግነው በርካታ ኢትዮጵያዊያን የኩላሊት ንቅለ ተከላ ከማካሄዳቸው በፊት በሆስፒታሉ የኩላሊት ዕጥበትን እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል።

አቢሲንያ ባንክ በባለውለታ መርሃ ግብሩ በኩላሊት ህመም ለሚሰቃዩት የቀድሞው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገዥ ለነበሩት አቶ ዱባለ ጃሌ ለህክምና አገልግሎት የሚውል 1 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉም ተገልጿል።

በቁምነገር አሕመድ