አትሌት ዳዊት ስዩም አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዘገበች

ጥቅምት 28/2014 (ዋልታ) አትሌት ዳዊት ስዩም በ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዘገበች፡፡

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዳዊት ስዩም በፈረንሳይ ሊል በተካሄደ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ነው አዲስ የዓለም ክብረወሰን ያስመዘገበችው።

አትሌቷ ርቀቱን 14 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ የገባች ሲሆን፤ ከዚህ ደቀም በርቀቱ ተይዞ የነበረውን 14 ደቂቃ ከ43 ሰከንድ በ2 ሰከንድ በማሻሻል ነው ክብረወሰኑን በእጇ ያስገባችው።

አል-ዐይን እንደዘገበው በወንዶች በተካሄደው ውድድር ደግሞ አትሌት በሪሁ አረጋዊ 1ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡