አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከተመራቂ ተማሪዎች ጋር ተወያዩ

ነሃሴ 13/2013 (ዋልታ) – የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በ2013 ዓ.ም ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች ከተመረቁ ተማሪዎች ጋር ተወያዩ።

በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳይ ገለፃ ማድረግ፣ በክልሉ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ለተመራቂዎቹ የስራ እድል መንግሥት እያመቻቸ መሆኑንና ለተመራማሪዎቹ  በተለያዩ የስራ መስኮች የስራ እድል መፍጠር በሚቻልበት ዙርያ ውይይቱ ተካሂዷል።

ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ መንግሥት ለተመራቂዎቹ የስራ እድል ለመፍጠር ዝግጁ እንደሆና ተመራቂዎቹም በሚመደቡበት ቦታ ሁሉ ለህዝባቸው በቅንነት ማገልገል እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ከለውጡ በኋላ በክልሉ በልማት በተለይ በትምህርት፣ በጤናና በመንገድ ዘርፎች ብዙ አመርቂ ስራዎች እንደተሰሩ ተናግረው፣ የክልሉ ሰላምም በአስተማማኝ ሁኔታ ተረጋግጧል ብለዋል።

ከሶስት ሺህ 500 በላይ አዳዲስ ተማሪዎች የስራ እድል ለመፍጠር መዘጋጀቱን የሶማሊ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ አብዱልቃድር አብዲ መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

በተለያዩ የስራ መስኮች 120 ሺህ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር መታሰቡን በውይይቱ ተገልጿል።