አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ በክልሉ ከሚገኙ የግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር ተወያዩ

                           አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ

ሰኔ 24/2013 (ዋልታ) – የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙመድ በክልሉ ከሚገኙ የግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸው የመንግስትና የግብረሰናይ ድርጅቶች ግንኙነት መጠናከር፣ የአፋጣኝ ምላሽ መስጠት እቅድና ዝግጅት፣ በክልሉ ባሉ ጫናዎችና ችግሮች ዙሪያ መክረዋል።

በክልሉ በድርቅ፣ በጎርፍ አደጋና ግጭት ከቀያቸው በተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ዙሪያም በውይይት መድረኩ የተለያዩ ሀሳቦች ተነስተዋል፡፡

በአለም አቀፍ ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተከሰተው ኮቪድ-19ና የዋጋ ንረት አማካኝነት በክልሉ የሚገኙ አቅማቸው አነስተኛ የሆኑ ዜጎችን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ፈተና መሆኑም በመድረኩ ተንፀባርቋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በክልሉ ዘንድሮ የዝናብ እጥረት ሊኖር ስለሚችል የግብረሰናይ ድርጅቶች ከክልሉ መንግስት ጋር በመቀናጀት ድርቅ ከመከሰቱ ቀደም ብሎ ዝግጅቶች እንዲጠናከሩ ማድረግ እንዳለባቸው አቶ ሙስጠፌ መናገራቸውን ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡