አና ጎሜዝ ህወሓት ህፃናትን ለሽብር ተግባር ማሰለፉ አሳዛኝ ድርጊት መሆኑን ገለፁ

ሐምሌ 08/2013 (ዋልታ) –  በአውሮፓ ህብረት በፓርላማ አባልነት ለ15 ዓመታት ያገለገሉት አና ጎሜዝ አሸባሪው ህወሓት ህፃናትን ለሽብር ተግባር ከፊት ማሰለፉ አሳዛኝ ድርጊት መሆኑን ገለፁ፡፡
አና ጎሜዝ በትዊተር ገጻቸው “ሰላም፣ ዴሞክራሲ እና እውነተኛ ልማት እውን እንዲሆን ፅኑ ምኞት እንዳለኝ ለኢትዮጵዊያ ይድረሳቸው” ብለዋል፡፡
አና ጎሜዥ በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የፖርቹጋል ተወካይ ሲሆኑ በ1997ቱ ሀገራዊ ምርጫ ህብረቱን በመወከል የኢትዮጵያን ሀገራዊ ምርጫ መታዘባቸው ይታወቃል፡፡ ከዛን ጊዜ ጀምሮ አና ጎሜዝ የኢትዮጵያን ፖለቲካን በቅርበት እየተከታተሉ አስተያየት በመስጠት ይታወቃሉ፡፡