አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ዳግም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ ሆነው ተመረጡ

ሰኔ 11/2013(ዋልታ) – የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለሁለተኛ ጊዜ ድርጅቱን በዋና ፀሀፊነት እንዲያገለግሉ በድጋሚ መመረጣቸውን ድርጅቱ  አስታውቋል።

“ለሁለተኛ ጊዜ የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ ሆኜ እንዳገለግል እምነታቸሁን ስለጣላቸሁበኝ ክብር ይሰማኛል  የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ማገልገል ታላቅ ነገር ነው” በማለት በትዊተር ገጻቸው የተሰማቸውን ከፍተኛ ክብር እና ምስጋና ገልጸዋል፡፡

የቀድሞው የፖርቹጋል ጠቅላይ ሚኒሥትር አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ ሆነው በመጀመሪያ የተመረጡት የዛሬ 5 ዓመት እኤአ 2016 ነበር።