አዋሽ ባንክ የትምህርት አስተዳደር ስርዓት የሚያሻሽል ዲጂታል ሲስተም አስጀመረ

ሐምሌ 7/2014 (ዋልታ) አዋሽ ባንክ የዲጂታል ትምህርት አስተዳደር ስርዓት መተግበር ያስችላል የተባለው የኢ ስኩል ሲስተም (E school management system) አስጀመረ።

ይህም የትምህርት ቤት አስተዳደር፣ የመረጃ አያየዝ እና የክፍያ ስርዓትን ከማንዋል ወደ ዲጂታል ይቀይራል ተብሏል።

የተማሪዎችን መረጃ በቀላሉ ከማግኘት ባለፈም ከወረቀት የፀዳ አሰራር መሆኑ ተገልጿል።

ኢ ስኩል ሲስተም ለትምህርት አስተዳደር ፣ ለተማሪዎች እና በዘርፉ ለተሰማሩ የላቀ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በሚኪያስ ምትኩ