አየር መንገዱ በ2021 ግዙፉን የኤርባስ 350 አውሮፕላን በብዛት በመጠቀም ከቀዳሚዎቹ ተርታ ተሰለፈ

ታኅሣሥ 25/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጎርጎሮሲያኑ 2021 እጅግ ዘመናዊና ግዙፉን የኤርባስ 350 አውሮፕላን በብዛት በመጠቀም በዓለም ከቀዳሚዎቹ አየር መንገዶች ተርታ መሰለፉ ተገለፀ።
አየር መንገዱ የኤርባስ 350 አውሮፕላኖችን በመጠቀም በ2021 ዓመት 6 ሺሕ 500 በረራዎችን ማድረጉ ተጠቅሷል።
በዚህም ግዙፉን ኤርባስ 350 በብዛት በመጠቀም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ30 አየር መንገዶች 5ኛ ደረጃን ይዟል።
ምንም እንኳን አየር መንገዱ በዋናነት የቦይንግ አውሮፕላኖችን በመጠቀም የሚታወቅ ቢሆንም ለደንበኞቹ አማራጭ በመስጠት ውጤታማ ነበር ተብሏል።
በዓመቱ የኤርባስ 350 አውሮፕላንን በመጠቀም ከ28 ሺሕ በላይ በረራዎችን ያደረገው የኳታር አየር መንገድ የመጀመሪውን ደረጃ መያዙን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።