አየር ኃይሉ አሸባሪውን የሕወሓት ቡድን ድባቅ እየመታ ነው

ጥቅምት 25/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ አየር ኃይል ከመቼውም ጊዜ በላይ አሸባሪውን የሕወሓት ቡድን ድባቅ ለመምታትና ስርዓተ ቀብሩን ለመፈፀም የሚያስችል ሥራ በብቃት እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምክትል አዛዥና የሎጅስቲክ አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ነገራ ሌሊሳ ለኢፕድ እንደገለጹት አየር ኃይሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ አሸባሪውን የሕወሓት ቡድን ድባቅ ለመምታትና ስርዓተ ቀብሩን ለመፈፀም የሚያስችል ሥራ እየሠራ ነው።

ተቋሙን በቴክኖሎጂም ሆነ በሰው ኃይል አደረጃጀት አቅሙን ለማሳደግ ከሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት ጎን ለጎን በሀገር ላይ የተቃጣውን ወረራ ለማክሸፍም አኩሪ ተግባርና ታላቅ ጀብዱ እየፈፀመ መሆኑን አስረድተዋል።

አየር ኃይሉ የአሸባሪው ሕወሓት ቡድንን ሞት እንዲፋጠን የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን ገልጸው የአሸባሪ ኃይሉን እንቅስቃሴ እየተከታተለ ድባቅ እየመታው እንደሚገኘም ተናግረዋል።