አደንዛዥ ዕፅ ለማዘዋወር የሞከረ ግለሰብ ተያዘ

ሚያዝያ 12/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ አደንዛዥ ዕፅ በሻይ ቅጠል ደብቆ ለማዘዋወር የሞከረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ለዋልታ በላከው መረጃ እንዳስታወቀው ግለሰቡ በቁጥር 107 ፍሬ የሚሆን አደንዛዥ ዕፅ ለማዘዋወር በዝግጅት ላይ እያለ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ወደ አማራ ክልል ጎንደር አካባቢ ለመውሰድ እቅድ የነበረው ግለሰቡ በየካ ክፍለ ከተማ ላምበረት አካባቢ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ መያዙ ተጠቁሟል፡፡