አዲስ አምባሳደሮች ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሥራ መመሪያ ተቀበሉ

የካቲት 18፣ 2013 (ዋልታ) – በተለያዩ አገራት የተሾሙ አዲስ አምባሳደሮች ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሥራ መመሪያ ተቀብለዋል፡፡

በወቅቱም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን አምባሳደሮቹ በኢትዮጵያና በተሾሙበት አገር መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንዲተጉ አሳስበዋል፡፡

ተሿሚ አምባሳደሮቹ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ አማካኝነት ቃለ-መሀላ መፈጸማቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡