አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ ለኅዳሴ ግድብ ከ1.5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

የካቲት 25/2014 (ዋልታ) “ስጦታችን ለግድባችን” በሚል አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ ለታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ግንባታ 1 ሚሊየን 561 ሺሕ 457 ብር ድጋፍ አድርጓል።
ባንኩ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት የራሱን አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን ደንበኞች ከውጭ ሀገር የሚላክላቸውን ገንዘብ በባንኩ እንዲመንዝሩ በማድረግ የተገኘውን ገቢ ለኅዳሴ ግድብ እንዲውል ማደረጉ ተገልጿል።
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) ድጋፉ የኅዳሴ ግድብ ግንባታ በታቀደለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ እንደሚያደርግ አውስተዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ እየሰራ ይገኛል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ግድቡን ገድበን በሥራ ላይ ለማዋል መተባበር አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።
በዙፋን አምባቸው