አዲስ የሚመሰረተው መንግስት በፀጥታና በኢኮኖሚ መረጋጋት ላይ ያለው የቤት ሥራ

በወሎ ዩኒቨርሲት የፍልስፍና መምህር ዮናስ መኮንን

መስከረም 5/2014 (ዋልታ) መስከረም ወር መጨረሻ ላይ የሚመሰረተው አዲስ መንግስት የሀገርን ፀጥታ ችግሮች በመፍታትና ኢኮኖሚውን በማረጋጋት ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚኖርበት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ምሁር ገለጹ፡፡

በተለይ በሰሜን፣ በምዕራብ ኦሮሚያና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልና ተመሳሳይ ችግሮች ባሉባቸው ሀገሪቱ ክፍሎች የፀጥታና የኢኮኖሚ መረጋጋት ለማስፈን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትከረት አድርጎ መስራት እንዳለበት መምህር ዮናስ ተናግረዋል፡፡

በወሎ ዩኒቨርሲት የፍልስፍና መምህር ዮናስ መኮንን መንግስት የኢኮኖሚ ዕድገትን በሚያረጋጉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ይጠበቅበታልም ብለዋል፡፡

እንደ መምህር ዮናስ ገለጻ መንግስት ውስጣዊ ችግሮችን በመፍታት ፀጥታና ደህንነትን ከማረጋገጥ ቀጥሎ ቀጣናዊ መረጋጋት ላይ ትከረት መደረግ አለበት፡፡

ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያና ሱዳን መካከል ያለው ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ለማድረግ በሚያስችሉ ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ላይም አተኩሮ መስራት ይገባል ሲሉ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል፡፡