አፈጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በአሴካ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ

አፈጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በአሴካ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ
አፈጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በአሴካ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ

የካቲት 24/2014 (ዋልታ) በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አገኘሁ ተሻገር የተመራና በአሴካ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ሞሮኮ ራባት የገባው ልዑክ በጉባኤው እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

በአሴካ (Association of Senates, Shoora and Equivalent Councils in Africa and the Arab World) ጉባዔ ላይ ናይጄሪያ፣ ቡሩንዲ፣ ግብፅ፣ ሞሪታኒያ፣ ሱዳን፣ ሳኡዲ አረቢያ፣ ባህሬን፣ የመን፣ ጆርዳን እና ሌሎች አገራት የሚሳተፉ ሲሆን በርካታ የአፍሪካ እና የአረብ አገራት በአባልነት የታቀፉ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
በአሁኑ ሰዓት በአፈጉባዔ አገኘሁ የተመራው የልዑካን ቡድን በጉባዔው ላይ እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረቡ ዓለም አገራት የተወጣጡ ተሳታፊዎችም በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል።
አፈጉባዔ አገኘሁ በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም በተለይም በአየር ንብረት ለውጥ፣ ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ፣ ሰለታላቁ የኅዳሴ ግድብና የጋራ ተጠቃሚነት እንዲሁም በአፍሪካና በአረቡ ዓለም አገራት መካከል ሊኖር ስለሚገባው ነጻ የንግድ ቀጣና እና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት አድርገዋል፡፡
የዚህን ጉባዔ መድረክ አፈጉባኤ አገኘሁ በምክትል ፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ በጉባኤው በመመረጣቸው መድረኩን እየመሩ እንደሆነም የምክር ቤቱ መረጃ አመላክቷል።