ኢትዮጵያና ጅቡቲ የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናል ሊገነቡ ነው

ሚያዝያ 27/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በጅቡቲ ዳማርጆግ የኢንዱስትሪ ፓርክ የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናል ሊገነቡ መሆኑ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማሞ ምህረቱና የጅቡቲው ግሬት ሆርን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ፕሬዝዳንት አቡበከር ኦማር ሃዲ ተርሚናሉን ለመገንባት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ አገራቱ በቀጣይ ተመሳሳይ የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናሎችን በጥምረት ለማልማት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ከጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።