ኢትዮጵያና ፖርቹጋል የኢንቨስትመንት ግንኙነታቸውን ለማጠናከር የሚስችል ውይይት አደረጉ

ግንቦት 8/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ እና የፖርቹጋል አምባሳደር ሊዊሳ ፋርጎሶ የሁለቱን አገራት የኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይታቸውም የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት በማስተዋወቅ የፖርቹጋል ባለሀብቶችን ወደሀገራችን ለመሳብ ከስምምነት ላይ መደረሱን የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡