ኢትዮጵያዊያን በኔዘርላንድስ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ታኅሣሥ 7/2014 (ዋልታ) በኔዘርላንድስ ዴን ሃግ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ።

ሌሊቱን የተካሄደው ይህ ሰልፍ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የመግባት ፍላጎት ያላቸውን የውጭ ኃይላት በመቃወም ሲሆን የበቃ #Nomore ንቅናቄ አካል ነው።

ሰልፈኞቹ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረጉ የምጣኔ ሃብትና የፖለቲካ ጫናዎችን ተቃውመዋል።

የተንሸዋረረ የውጭ መገናኛ ብዙኃን ዘገባን ያወገዙም ሲሆን የኢትዮጵያ እውነት በመካድ ዓለምን የተሳሳተ አረዳድ እንዲኖረው ለማድረግ ከማሴር እንዲታቀቡም መገናኛ ብዙኃኑን ጠይቀዋል።

በተያያዘም አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት በአፍሪካ መሪዎች የተጀመረውን ጥያቄም አስተጋብተዋል።