መስከረም 20/2016 (አዲስ ዋልታ) በ5ኪሎ ሜትር የወንዶች የዓለም የጎዳና ላይ የፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች 1ኛ እና 2ኛ ተከታትለው መግባት ችለዋል፡፡
ውድድሩን አትሌት ሀጎስ ገብረ ህይወት 12:59 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ 13:02 በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
ከሰዓታት በፊት በተደረገ በሴቶች የ5 ኪሎ ሜትር የሪጋ የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ አትሌት እጅጋየሁ ታዬ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች፡፡