ኢትዮጵያዊ የአንድነት መንፈስን በማጥበቅ በዓለም አደባባይ ድምፅ በመሆናችሁ በእጅጉ እናመሰግናለን – ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን

ጳጉሜ 2/2014 (ዋልታ) ”ኢትዮጵያዊ የአንድነት መንፈስን በማጥበቅ በዓለም አደባባይ ድምፅ በመሆናችሁ በእጅጉ እናመሰግናለን፤ ኮርተንምባችኋል” ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በወራሪ ቡድኑ ዳግም የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በዋሽንግቶን ዲሲ – አሜሪካ የሚኖሩ ወገኖች እንደተለመደው እውነታውን ያስተጋቡበት ሰላማዊ የድጋፍ ሰልፍ በእጅጉ የሚደነቅ ነው ብለዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ኢትዮጵያዊ የአንድነት መንፈስን በማጥበቅ በዓለም አደባባይ ድምፅ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን አመስግነዋል።