ጥቅምት 14/2017 (አዲስ ዋልታ) ኢትዮጵያ የሰው ሕይወት በቀጠፈው እና አንካራ በሚገኘው የቱርክ ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪ ላይ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት ማዘኗን ገለጸች።
ለጥቃቱ ሰላባ ለሆው ወንድም የቱርክ ህዝቦች እንዲሁም ለወዳጅ የቱርክ መንግስት የተሰማትን ጥልቅ ሃዘን ገልፃለች።
ኢትዮጵያ የሽብር ጥቃቱን በጽኑ እነደምታወግዝና ሽብርተኝነት በመዋጋት ረገድ ከቱርክ ጎን መሆኗንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አስታውቋል።