ኢትዮጵያ በግብርናና ቱሪዝም ዘርፎች ከሞሮኮ ጋር ጠንካራ ትብብር ማድረግ  እንደምትፈልግ  ገለጸች

ጥር 26/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያ በግብርና እና ቱሪዝም ዘርፎች ከሞሮኮ ጋር ጠንካራ ትብብር ማድረግ እንደምትፈልግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለፁ።

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የኢትዮጵያን እና ሞሮኮን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከሞሮኮ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናስር ቡሪታ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።

በዚህም ከሞሮኮ ጋር ከግብርና እና ቱሪዝም ዘርፎች በተጨማሪ በሁለትዮሽ፣ አኅጉራዊ እና ዓለም ዐቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከርም ውይይት አድርገዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን ከ40ኛው የአፍሪካ ኅብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ጎን ለጎን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ አገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን እንደቀጠሉ ከሚኒስቴሩ ቃልአቀባይ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

 

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://www.facebook.com/waltainfo

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!